መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለሕሊናከ ዘመከረ በልባዌ። በሞቱ ወበተንሥኦቱ ለተሳትፎ መርዓዌ። ዓቃቤ ሥራይ ጊዮርጊስ መፈውሰ ደዌ። ለወለት ከመ ቤዘውካ እምአፈ ደራጎን አርዌ። ተረፈ ሕይወትየ ቤዙ እምኲሉ ምንሳዌ።
ዚቅ
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል : ወይቤ እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል።
ትርጉም
ጊዮርጊስ በታላቅ ቃል አምላኬ በዕፀ መስቀል ላይ እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም እያለ ጮኸ ።
ትርጓሜ
ስድስት ሰአት በሆነ ጊዜ ጊዮርጊስ ራሱን ዝቅ አደረገ መንፈሱም ያን ጊዜ ወጣች ።
ዚቅ ዓዲ (ወይም)
ሰኪቦ ለወልድ ትንሣኤ ሞቶ : ጊዮርጊስ ወረሰ ሰማያዊተ መንግሥቶ።
ትርጉም
ጊዮርጊስ የወልድ ትንሣኤ ሞቱን አስተምሮ ሰማያዊ የሆነች መንግሥቱን ወረሰ ።
https://t.me/EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ።
ትርጉም
ጊዮርጊስ በምስክር አደባባይ ላይ በግልጥ ቆሞ የበግዕ ክርስቶስ የሞቱን ትንሣኤ አስተማረ ።
ወረብ
ወይቤ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
https://t.me/EOTCmahlet
ዓዲ (ወይም)
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ወይቤ በዓቢይ ቃል/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
ትርጉም
ጊዮርጊስ በታላቅ ቃል አምላኬ በዕፀ መስቀል ላይ እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም እያለ ጮኸ ።
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለፀዓተ ነፍስከ ጽዋዓ ደመ ስምዕ ሰሪቦ። እማኅፈደ ሥጋ በገድል መከራ ስቃይ ድኅረ ረከቦ። ጊዮርጊስ ስመከ ሶበ እጼውእ በአስተርክቦ። ረድኤትከ ኀበ ሀሎኩ በአርአያ ብእሲ ቀሪቦ። ለትካዘ ልብየ ዘልፈ ያሰስል ዕፅቦ።
ዚቅ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።
ስድስት ሰአት በሆነ ጊዜ ጊዮርጊስ ራሱን ዝቅ አደረገ መንፈሱም ያን ጊዜ ወጣች ።
ወረብ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት "ጊዜ"/፪/ ፮ቱ ሰዓት/፪/
አጽነነ ርዕሶ ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ/፪/
ትርጓሜ
ስድስት ሰአት በሆነ ጊዜ ጊዮርጊስ ራሱን ዝቅ አደረገ መንፈሱም ያን ጊዜ ወጣች ።
https://t.me/EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ እምርጢነ ገለአድ ዘተኃርየ። በላዕለ ድውያን ፈወሰ እስመ ፈድፋደ አርአየ። ጊዮርጊስ ለከ ትብለከ ነፍስየ። በበድነ ሥጋከ ተማኅጸንኩ ኢታስተኀፍር ተስፋየ። ስዕለተ ከናፍርየ ስማዕ ወፈጽም ጻህቅየ።
https://t.me/EOTCmahlet
ዚቅ
ፈወሰ ዱያነ ወከሠተ አዕይንት ዕውራን : ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ ጊዮርጊስ ሰማዕት።
ትርጓሜ
ሰማዕት ጊዮርጊስ ሕመምተኞችን ፈወሰ ። የዕውራን ዐይንንም አበራ ። ሁሉን ፈጽሞ አረፈ ።
https://t.me/EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዕደ አግብርቲከ ፪ኤ። ድኅረ ሰለጥከ መዊተ እንዘ ብከ ተስፋ ትንሣኤ። ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ዓመታት ሱባኤ። ስመከ በተአምኖ ሶበ አወትር ጽዋዔ። አስራበ ረድኤትከ ያጥልል ዘዚአየ ጒርኤ።
https://t.me/EOTCmahlet
ዚቅ
፯ ዓመተ ዘኮነንዎ : ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት : ብእሲ ጻድቅ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።
ትርጉም
ቅዱስ ጊዮርጊስን ሰባት ዐመታትን ቢፈርዱበት እግዚአብሔር የመረጠው ጻድቅ ሰው እንደ አንዲት ቀን አልመሰለውም ።
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብሪከ ምክሐ አድያሚሃ ወዓጸዳ። ለምድረ ሙላድከ ልዳ። ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ። ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓውዳ። በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።
https://t.me/EOTCmahlet
ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር : ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ : ጸሎቱ ለጊዮርጊስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።
ትርጉም
ብርሃን ወደ እግዚአብሔር ሰው መቃብር ላይ ወረደ ። መቃብሩም ለሕመምተኞች ሕይወትን የሚሰጥ ሆነ ። የጊዮርጊስ ጸሎቱ ከበረከቱ ጋራ ከእኛ ጋረሠ ይኑር ።
ምልጣን
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ ሰማዕት : ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል : አማን ኃያል ገባሬ ኃይል።
ትርጉም
በቢላዋ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቆረጥ ከነገሥታት ዛሬ ተጻፈ ። ጊዮርጊስ ጸለየ በእሳትም አቃጠላቸው ። በእውነ፦ ኃይልን የሚያደርግ ኃያል ነው ።
አመላለስ
አማን በአማን ኃያል 'አማን በአማን'/፪//፪/
ኃያል ገባሬ ኃይል/፬/
ትርጉም
እውነት በእውነት ኃያል ነው እውነት በእውነት ኃይልን የሚያደርግ ኃያል ነው ።
ወረብ፦
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ/፪/
ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል አማን ገባሬ ኃይል/፪/
ትርጉም
በቢላዋ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቆረጥ ከነገሥታት ዛሬ ተጻፈ ። ጊዮርጊስ ጸለየ በእሳትም አቃጠላቸው ። በእውነ፦ ኃይልን የሚያደርግ ኃያል ነው ።
https://t.me/EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ወሰበረ ኆኃተ ብርት ሞዖ ለሞት : ተንሥእ ወልድ በሣልስት ዕለት : ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን እምጽልመት ወጽላሎተ ሞት : ካዕበ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ : ገሊላ እቀድመክሙ።
ትርጉም
የብረት ደጆችን ሰበረ ። ሞትን አሸነፈው ወልድ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ። ከሞት ጥላ እና ከጨለማ የጻድቃን ነፍስን ነጻ አወጣ ። ዳግመኛም ደቀ መዛሙርቱን ወደ ገሊላ እቀድማችሗለሁ አላቸው ።
እስመ ለዓለም (ዓዲ)
ንግበር በዓለ በትፍሥሕት :በአስተሐምሞ ቅድስተ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለጊዮርጊስ ነገሮ ኅቡዓተ ኲሎ ሥርዓተ ምሥጢር በደኃሪ ይትገበር ዘሀሎ በንዝኃተ ደሙ ለክርስቶስ ለመፃጉዕ ዘአሕየዎ በቃሉ ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ ተንሥአ እሙታን ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወለያዕቆብ ዘአዕተዎ ብሔሮ ተንሥአ እሙታን ምዕረ ሦዓ ርእሶ ወተዓውቀ በመንፈሱ በፈቃዱ ወልድ አቅተለ ርእሶ ተንሥአ እሙታን ሲኦለ ወሪዶ ሰበከ ግዕዛነ በመስቀሉ ወልድ ገብረ መድኃኒተ ተንሥአ እሙታን ጸርሐት ሲኦለ ወትቤ ሰማያዊ ዝስኩ ዘለኪፎቶ ኢይክል።
ትርጉም
የትንሣኤውን ማሰብያ የተለየች ፋሲካን በማዘጋጀት በደስታ በዓልን እናድርግ ። ለጊዮርጊስ የተሸሸገውን ሁሉ ነገረው ። በክርስቶስ በደሙ መረጨት ያለ የምሥጢር ሥርአት በመጨረሻ ይሠራ ። በቃሉ መጻጕዕን ያዳነው ለዕውር ዓይኑን ያበራለት ከሙታን ተነሣ ። አልዓዛርን ከሙታን ተነሳ ያለው ፤ ያዕቆብን ወደ አገሩ ያስገባው ከሙታን ተነሣ ።አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አደረገ ። በመንፈሱ ታወቀ ወልድ በፈቃዱ ራሱን አስገደለ ። ከሙታን ተነሣ ። ወደ ሲኦል ወርዶ ነጻነትን ሰበከ ። ወልድ በመስቀሉ መድኃኒትን አደረገ ። ከሙታን ተነሣ ። ሲኦል መንካቱን የማይችል ያው ሰማያዊ እያለች ጮኸች ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨