የማቴዎስ 28.19 ትውፊታዊ ንባብ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የታመነ እና ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ "በአብ፣በወልድ፣በቅዱስ መንፈስ" የሚለው ትዕዛዝ ያውቁ እንደነበር ነው የምንርዳው ፣ በተጨማሪም በዚህ ክፍል ትክክለኛነት ላይ ምንም ዓይነት ክርክር አላገኘሁም። በማቴዎስ 28፡19 ያሉት ሁሉም የግሪክ ቅጂዎች ትውፊታዊ ንባብን የያዙ ብቻ ሳይሆን፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሁሉ የሚጠቅሱት ወይም የሚጠቀሙት እንደሆነ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ብዙ ልጽፍ አስቤ ነበር ነገር ግን የጀመርኳቸው ርዕሶች ስላሉ አሁን ላይ እነርሱን መጨረስ ስላለብኝ በዚህ ጉዳይ ላይ ሜቴ 28:19 በጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድ ይታወቅ እንደነበረ ብዙ ማስረጃዎች አሉ ይህ ደግሞ ክፍሉ ጭማሪ ላለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ለጊዜው ማስረጃዎቹን ብቻ ላስቀምጥላችሁና ሌላ ጊዜ በሰፊው እንሄድበታለን።
Didache (a.d. 60-150) chapter 7.1-4
“Now about baptism: this is how to baptize. Give public instruction on all these points, and then baptize in running water, in the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit. If you do not have running water, batpize in some other. If you cannot in cold, then in warm. If you have neither, then pour water on the head three times in the name of the Father, Son, and Holy Spirit. Before baptism, moreover, the one who baptizes and the one being baptized must fast, and any others who can. And you must tell the one being baptized to fast for one or two days beforehand.”
"አሁን ስለ ጥምቀት፡ መጠመቅ እንደዚህ ነው፡ በእነዚህ ሁሉ ነጥቦች ላይ ለሕዝብ አስተምህሮ፡ ከዚያም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም በሚፈስ ውኃ አጥመቅ"
First Apology by Justin Martyr (a.d. 155) chapter 61
“…Then they are brought by us where there is water, and are born again, for they then receive washing in water in the name of God the Father and Master of all, and of our Savior Jesus Christ, and of the Holy Spirit. For Christ also said, ‘Except you are born again, you will not enter into the Kingdom of Heaven.’…”
"እንግዲህ ውሃ ወዳለበት ወደ እኛ አምጥተው ይወለዳሉ ዳግመኛም ይወለዳሉ፤በእግዚአብሔር አብና የሁሉ ጌታ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ መታጠብን ይቀበላሉና።ክርስቶስ ደግሞ፡- ዳግመኛ ካልተወለዳችሁ በቀር ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም ብሎአልና።"
Against Heresies by Irenaeus (a.d. 180) book 3 chapter 17.1
“…And again, giving to the disciples the power of regeneration into God, he said to them, ‘Go and teach all nations, baptizing them in the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit.’…”
"ዳግመኛም ለደቀ መዛሙርቱ ወደ እግዚአብሔር የመታደስ ኃይልን ሰጣቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው።"
On Baptism by Tertullian (a.d. 198) chapter 13
“For the law of baptizing has been imposed, and the formula prescribed: ‘Go,’ He saith, ‘teach the nations, baptizing them into the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit.’ The comparison with this law of that definition, ‘Unless a man have been reborn of water and Spirit, he shall not enter into the kingdom of the heavens,’ has tied faith to the necessity of baptism.”
"የማጥመቅ ሕግ ተጥሎበታልና፥ ቀመርም ተጽፏል፡- ሂዱ ይላል አሕዛብን አስተምራቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው።"ከዚህ ፍቺ ሕግ ጋር ንጽጽር 'ሰው ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም ጥምቀት ከእምነት ጋር የተሳሰረ ነው።"
https://t.me/Astemeheroteewnet