ቅዱስ ቁርባን : ለሉተራዊ አቋም መፅሐፍ ቅዱሳዊ ሙግት (Vindicating the Lutheran Doctrine of the Lord’s Supper)
Part 5
እስከ ክፍል አራት ድረስ በቅዱሳት ምስጢራት ላይ ያሉትን የካቶሊክና የሪፎርምድ አቋሞች ከነሙግቶቻቸው አቅርቤ ቀጥዬ ደግሞ ለምን ስህተት ናቸው ብለን እንደምናስብ ሙግቶችን አስቀምጫለሁ። በዚህ ውስጥ የካቶሊኩን Transubstantiation ስሞግት የህብስቱንና ወይኑን Substantial መገኘት አሳይቻለሁ ፤ ሪፎርምዱን ስሞግት የክርስቶስን ስጋ Substantial መገኘት አሳይቻለሁ። የሉተራኑ አቋም ደግሞ ሁለቱም ህብስቱና ስጋው ወይኑና ደሙ ይገኛሉ የሚል ስለሆነ ለካቶሊኩና ለሪፎርምዱ በቀረበው ወቀሳ ውስጥ በተዘዋዋሪ የሉተራኑ ሙግት (Positive Case) ተቀምጧል ማለት ነው።
ምንምኳ አስቀድሜ በመግበያዬ የዚህ አርቲክል አላማ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ሙግት ማቅረብ ብቻ እንደሆነ ባስቀምጥም ነገር ግን በዚህ ርዕስ ስር ለብዙዎች ግራ መጋባት ምክንያት የሆነው ይህ የሉተራን የቅዱስ ቁርባን ትምህርት ከGenus Magestaticum ጋር ያለው ግንኙነትና በእርሱም በኩል የሚሰጠው ማብራሪያ ስለሆነ ይህን ርዕስ ከመዝጋቴ በፊት በእርሱ ላይም ትንሽ ለማለት አሰብኩ። ምንምኳ ለእውነትነቱ ሙግት ባላቀርብም ነገር ግን ለቀጣይ ስራዎች መሰረት የሚሆን መግቢያ ሰጣለሁ።
በዚህ ክፍል ቀጣዮቹ ሶስት ሀሳቦች ላይ በመጠኑ ለመዳሰስ ሞክራለሁ።
1. What is not GM ?
2. What is GM ?
3. are Chalcedon and Constantinople contra GM ?
1. What is not GM ?
Genus Magestaticum ሶስት እንደስማችን ልንሸመድዳቸው የሚገቡ ነገሮችን አይደለም። ብዙ ጊዜ ብዙዎች ላይ የማየው ችግር እነዚህን ካለመረዳት የሚመጣ ነው። እነዚህም ናቸው፦
A. Not by Subjective Inherence
የመለኮታዊ ባህሪያቱ የሰውነቱ Substantial-ም ሆነ Accidental Property አይደሉም። ሰውነቱ ባህሪውን Formally, Essentially or Intrinsically አልያዘውም።
B. Not by multiplication of itself and Not by Duplication
የሰውነት ባህሪው የሆነው ስጋው በብዙ ቦታ የመገኘትን የመለኮቱን ባህሪ ሲቀበልና ሲያስተላልፍ የስጋን አካል በመጨመር ወይም በማባዛት ያደረገው አይደለም። እንዲሁም የሰውነት ባህሪው የያዘው የመለኮቱ ባህሪ ከተቀበለበት ከመለኮቱ ባህሪ የተነጠለና በራሱ የሚቆጠር አይደለም ማለት ነው።
C. Not by Transfusion
የመለኮት ባህሪያት ከሚቀመጡበትን አካል እየተነቀሉ ወይም እየተው አይደለም ወደ የሚተላለፉት። ሁለቱም ባህሪያት ያላቸውን Essential and intrinsic ባህሪ አልጣሉም አልተውም።
2. What is GM ?
“Another distinction is this. In some of the bodies which are called hot [predication] the heat is derived from without, while in others it belongs to the bodies themselves; and it makes a most important difference whether the heat has the former or the latter origin… For the actual substratum may not itself be hot, but may be hot when coupled [συνδυαζόμενον] with heat as an attribute, as would be the case if one attached a single name to hot water or hot iron. It is after this manner that blood is hot.”
Aristotle, On the Parts of Animals, bk. II, ch. ii
“Communication according to coupling is that which happens according to the association of two diverse natures through which one of the united things is connected with the other in such a way that, while the essence remains distinct, nonetheless the one truly receives and puts on the property, force, and efficacy of the other without any confusing, through and because of the communion that has occurred. We have examples in the fiery iron and the body endowed with Soul.”
Gerhard, Exegesis, Loc. 4, 175
አርስቶትል ባስቀመጠው ፤ ገርሀርድም ቀጥታ ከእርሱ በወሰደው በዚህ አቀማመጥ መሰረት ይህ እኛ Genus Magestaticum ብለን የምንጠራውን Communication by Coupling ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ሁለት ነገሮች በአንድነት በመቀመጣቸው ብቻ እያንዳንዳቸው ያላቸውን የየራሳቸውን ባህሪ ሳይጥሉና ወደሌላ ነገር Essentially ሳይቀየሩ ነገር ግን አንዱ በሌላኛው አብሮት ባለው ነገር ላይ የራሱን ባህሪ Exert የሚያረግበት ፤ ሌላኛውም እነዛን ባህሪያትና ተግባራት (operations) ተቀብሎ በራሱ ውሰጥ ወይም በኩል የሚያስተላልፍበት ነው።
አንድታስተውሉ የምፈልገው ይህንን Communication ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ አርስቶትል ድረስ ልንመዘው የምንችለው መሆኑንና ከዛም በላይ ደግሞ አርስቶትል ራሱ ለዚህ ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመው የጋለ በረትን መሆኑን ነው። መቼም የአርስቶትልንም የምሳሌውን አጠቃቀም Communicato Idiomaticum ነው ብለው ሪፍርምዶቹ እንደማይመልሱልን ተስፋ በማድረግ ልቀጥል።
3. Are Chalcedon and Constantinople opposed to GM ?
Genus Magestaticum ላይም ሆነ ቅዱስ ቁርባን ላይ ሪፎርምዶች ሉተራኑን ለመቃወም በተጋጋሚ የሚያነሱት ሙግት ከኬልቄዶን ጉባኤ ጋር ትጋጫላችሁ የሚል ነው። ከኬልቄዶን የሚጠቅሷት ክፈል ይህች ነች፦
‘.. one and the same Christ, Son, Lord, Only-begotten, recognized in two natures, without confusion, without change, without division, without separation; the distinction of natures being in no way annulled by the union, but rather the characteristics of each nature being preserved and coming together to form one person and subsistence, not as parted or separated into two persons, but one and the same Son and Only-begotten God the Word, Lord Jesus Christ.. ‘