ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድና ውሳኔ
===================
ትእዛዝ (order ) ,,,ብይን ( Ruling ) ,, ፍርድ (Judgement ),,ዉሳኔ ( Decision /Decree )
እነዚህ አራት ቃላት በሕግና በፍርድ ቤት የሥራ ሂደት ዉስጥ ተመሳሳይ ቢመስሉም የራሳቸው የሆነ የተለየ የሕግ ትርጉምና ደረጃ አላቸው ,,,,,,,,
1, ትእዛዝ ( Order )
" ትእዛዝ " ማለት አንድ የፍርድ ቤት ክርክር ከመጀመሩ በፊት ወይም በሂደት ላይ እያለ ፍርድ ቤቱ አንድን ነገር እንዲደረግ ወይም እንዳይደረግ የሚሰጠው መመሪያ ነው ።
ባህሪው
ጉዳዩ መዝጋት ወይም መጨረስ ሳይሆን ለሂደቱ መቀላጠፍ የሚሰጥ ነው ።
ለምሳሌ :
"ይህ ንብረት ለጊዜው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ታግዶል " ወይም " ተከሳሽ ለቀጣይ ቀጠሮ ምስክሮች ይዞ ይቅረብ " የሚሉ መመሪያዎች ትእዛዝ ይባላል ።
2, ብይን ( Ruling )
" ብይን" የሚሰጠው በክርክሩ ሂደት ዉስጥ ለሚነሱ መከራከሪያ ነጥቦች ( Interlocutory matters ) ምላሽ ለመስጠት ነው ።
ባህሪው
ዋናው የክርክር ዉጤት ( ማን አሸነፈ ? ማን ተሸነፈ ?) ሳይሆን በመሀል የሚነሱ የህግ ክርክሮችን ለመወሰን ነው ።
ለምሳሌ ;
" ፍርድ ቤቱ ይህንን ክስ ለማየት ስልጣን አለው / የለዉም " ወይም " ክሱ በይርጋ ይታገዳል / አይታገድም " የሚለው ዉሳኔ ብይን ይባላል ።
ብይን ብዙ ጊዜ ክርክሩን አያበቃዉም ይልቁንም ሂደቱን ይቀጥላል ።
3, ፍርድ ( Judgement )
" ፍርድ " ማለት ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃዎች መርምሮ ; የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶና መዝኖ የሚሰጥ የመጨረሻ ድምዳሜ ነው ።
ባህሪው
ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የደረሰበትን የሐቅና የህግ ድምዳሜ በዝርዝር የሚያስቀምጥበት ሰነድ ነው ።
ለምሳሌ ;
" ከሳሽ የንብረቱ ባለቤት መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል "
የሚለው ሰነድ ፍርድ ነው
4,ዉሳኔ ( Decision /Decree )
" ዉሳኔ " በፍርድ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ተግባራዊ ትዕዛዝ ነው ።
በፍርድ መደምደሚያ ላይ " በዚህ መሠረት ",,,,,,,,,ተብሎ የሚቀመጠው ነጥብ ነው ።
ባህሪው
በፍርድ የተረጋገጠውን መብት ወይም ግዴታ ለይቶ የሚያስቀምጥና ተፈፃሚ የሚሆን ነው ።
ለምሳሌ ;
ፍርዱ " ከሳሽ ባለቤት ናቸው " ካለ,,,,,
ዉሳኔዉ " ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ያስረክቡ" የሚለው የመጨረሻ ትዕዛዝ ነው ።
ማጠቃለያ / ልዩነት
/ቃል/ ትኩረት / መቼ ይሰጣል ?
# ትእዛዝ
ለስራ ሂደት መመሪያ መስጠት
በማንኛውም ጊዜ
# ብይን
በመሀል ለሚነሱ መከራከሪያዎች መልስ መስጠት
በሂደት ላይ
# ፍርድ
ማስረጃ መዝኖ ድምዳሜ ላይ መድረስ
በክርክሩ ማብቂያ
# ዉሳኔ
መብትና ግዴታን ለይቶ መወሰን
በፍርድ መጨረሻ
#ጠበቃ እስከዳር አወቀ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
https://t.me/Higehatet