የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Nursing, Human Nutrition, Optometry, Pediatric and Child Health Nursing, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health, Surgical Nursing, Anesthesia, Psychiatric Nursing, Pharmacy, Medical Radiology Technology, Midwifery, Medicine, Public Health, Medical Laboratory Science and Physiotherapy ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከነሀሴ 7 - 9/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦
(1) የፈተናው መርሃ-ግብር
- በ07/12/2017 ዓ.ም…… Pharmacy, Medical Laboratory Science Nursing, Dental Medicine, Pediatric and Child Health Nursing, Optometry and Surgical Nursing
- በ08/12/2017 ዓ.ም…… Nursing, Psychiatric Nursing, Emergency and Critical Care Nursing and Physiotherapy
- በ09/12/2017 ዓ.ም…
… Medicine, Public Health, Anesthesia, Midwifery and Medical Radiology Technology, Environmental Health and Human Nutrition
ሁሉም ተፈታኝ ነሀሴ 06/2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::
(2) በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
(3) ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎችን፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
(4) በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣
(5) ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እያሳሰብን:-
- ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘውን የፈተና ጣቢያዎች ዝርዝር መመልከት ይኖርባችኋል።
- ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
- በፈተና ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡