✍ሙሐመድ ወይስ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
እውነተኛው አገልጋይ ማን ነው?
ሙስሊሞች እንዲያውቁ ብለን እንጂ ጳውሎስ ክብር ከመሀመድ ጋር አይነፃፀርም !
ሙስሊም ወገኖቻችን ከሚነቅፏቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ስብዕናዎች መካከል ሐዋርያው ጳውሎስ በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የመጀመርያዎቹን የኢየሱስ ተከታዮች ትምህርት በማጣመም ክርስትናን የፈጠረ ሰው አስመስለው የሚስሉት ሲሆን ኢየሱስ ካስተማረው ትምህርት የተለየ ትምህርት ያስተማረ ሐሰተኛ ሐዋርያ ነው ይሉታል። ሙስሊም ወገኖች በሐዋርያው ጳውሎስ ላይ የከረሩ ትችቶችን መሰንዘራቸው ካለማወቅና ከአጉል ጥላቻ የመነጨ እንጂ በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ጥንታውያን ሙስሊሞች ሐዋርያው ጳውሎስ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ መሆኑን መመስከራቸውን መስማት ለዘመናችን ሙስሊሞች በእጅጉ አስደንጋጭ ነው።
ኢብን ኢስሐቅ የተሰኘው ቀዳሚውን የሙሐመድ ግለ ታሪክ የከተበ ሙስሊም እንዲህ ሲል ጽፏል፡-
“ዒሳ የመርየም ልጅ የላካቸው ደቀ መዛሙርትና ከእነርሱ በኋላ የመጡት በአገሪቱ ውስጥ የነበሩት እነዚህ ነበሩ፡- ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ደግሞ ጳውሎስ ወደ ሮም ተላኩ፡፡ (ጳውሎስ ከተከታዮቹ መካከል ሲሆን ደቀ መዝሙር አልነበረም፡፡) እንድርያስና ማቴዎስ ወደ በላዔ-ሰብዕ ምድር፤ ቶማስ በምስራቅ ወደሚገኘው ወደ ባቤል ምድር፤ ፊልጶስ ወደ ካርቴጅና ወደ አፍሪካ፤ ዮሐንስ የዋሻዎቹ ወጣቶች ምድር ወደሆነው ወደ ኤፌሶን…” (Alfred Guillaume. The Life of Muhammad: a Translation of Ibn Ishaq’s Sirat Rasul Allah, p. 653)
የኢብን ኢስሐቅ ጽሑፍ ሳሂህ አል-ቡኻሪና ሳሂህ ሙስሊምን ከመሳሰሉት ሐዲሳት እንኳ የሚቀድም የሙሐመድ ግለ ታሪክ ነው፡፡ በቅንፍ የተቀመጠው ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ደቀ መዝሙር እንዳልነበረ በትክክል የሚገልፅ በመሆኑ ስህተት የለበትም፡፡
የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈውን ከጠቀሰ በኋላ የአላህ ቃል መሆኑን መስክሯል፦
“ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን” (1ቆሮንቶስ 2፡9)፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ሐዋርያው ጳውሎስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሱትን የእግዚአብሔርን ተስፋዎች በራሱ አባባል ጨምቆ ያስቀመጠበት ዓረፍተነገር ሲሆን ከእርሱ በሚቀድም በየትኛውም ምንጭ ውስጥ በዚህ መልኩ ተጽፎ አይገኝም፡፡ ሙሐመድ እንዲህ ጠቅሶታል፡-
“አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፈው ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህ እንዲህ አለ ‹እኔ ለታማኝ ባርያዎቼ ዓይን ያላየችውን፣ ጆሮ ያልሰማውን የሰው ልብ ሊያስበው የማይችለውን (አስደናቂ ነገሮች)› አዘጋጅቻለሁ፡፡››” (Sahih Al-Bukhari, Vol. 9, Book 93, Number 589)
የዘመናችን ሙስሊሞች ከነቢያቸው በላይ አዋቂ ከሆኑ ይንገሩን፡፡
ለማንኛውም ከሐዋርያው ጳውሎስና ከሙሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ማን ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ጉዳዩ ሌላ ነው። ሙሐመድ ምንም ዓይነት የእውነተኛ ነቢይነት ምልክት ያልታየበትና እንዲያውም በተጻራሪው ከእግዚአብሔር ያልተላከ ሰው መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ አስደንጋጭ ተግባራትን የፈጸመ ሲሆን ሐዋርያው ጳውሎስ ግን ከአንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሚጠበቁ መልካም ፍሬዎችን አፍርቷል። እነሆ የተቀመጠውን ንፅፅር ይመልከቱ፦
ነቢዩ ሙሐመድና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ – ንፅፅር
ነቢዩ ሙሐመድሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
መሀመድ ነቢይነቱን ካወጀ በኋላ ነፍሰ ገዳይ ሆኗል፣ ነፍሰ ገዳይነትንም አስተምሯል ሱራ 4፡89፣ 5፡33፣ 33፡26፣ Sahih Muslim, 6985
ጳውሎስ የክርስቶስ ተከታይ ከሆነ በኋላ ስለ ቀድሞ ጥፋቱ ንስሐ ገብቷል 1ጢሞቴዎስ 1፡13-16
መሀመድ መድብለ ጋብቻን ፈፅሟል፣ የአክስትና የአጎት ልጆቹን አግብቷል (ሱራ 33፡50-52)፣ በአንድ ሌሊት ከ 9 ሴቶች ጋር ተኝቷል (Sahih al-Bukhari Vol. 7, Bk 62, No. 5)፣ እንዲሁም የ 6 ዓመት ህፃን አጭቶ በ 9 ዓመቷ አግብቷታል (Sahih al-Bukhari, Vol. 5 No. 234; Vol. 7 No. 65)
ጳውሎስ ለወንጌል አገልግሎት ሲል ከጋብቻ ታቅቦ ኖሯል (1ቆሮ. 7፡8)፣ የአንድ ለአንድ ጋብቻን አስተምሯል (1ጢሞ. 3፡2፣ 3፡12፣ ቲቶ 1፡6)
መሀመድ ሚስቶችን መምታት ፈቅዷል ሱራ 4፡34
ጳውሎስ ባል ሚስቱን እንደ ገዛ ሥጋው እንዲንከባከብ አስተምሯል ኤፌ. 5፡25-33
መሀመድ ባል ሚስቱን እንደ ግል እርሻው በመቁጠር እንዲደርስባት አስተምሯል ሱራ 2፡223፣ Sunan Abu Dawud Bk. 11, No. 2159
ጳውሎስ ባልና ሚስት አንዳቸው በሌላቸው አካል ላይ እኩል ሥልጣን እንዳላቸው አስተምሯል 1ቆሮ. 7፡1-5
መሀመድ ወንዶች ከሴቶች እንደሚበልጡ አስተምሯል ሱራ 2፡228፣ 4፡34 (ይህ ብልጫ የሥልጣን ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ጭምር ነው Tafsir Ibn Kathir Part 2, Abridge by Sheikh Muhammad Nasib, 1998, P. 204)
ጳውሎስ ወንዶችና ሴቶች እኩል እንደሆኑ አስተምሯል ገላቲያ 3፡28
መሀመድ አጋንንት ነበረበት Sahih al-Bukhari Vol. 4, Bk 53, No. 400; Bk 54, No. 490, Bk 71, No. 658, Sahih Muslim 39:6757
ጳውሎስ ሰዎችን ከአጋንንት ነፃ አውጥቷል ሐዋ. 16፡16-18፣ 19፡11-16
መሀመድ አንድም ተዓምር አላደረገም ሱራ 2፡118፣ 6፡37፣ 6፡109፣ 10፡20፣ 13፡7፣ 13፡27፣ 17፡59፣ 17፡90-93፣ 28፡48፣ 29፡49-51
ጳውሎስ ብዙ ተዓምራትን አድርጓል ሐዋ. 14፡3፣ ሮሜ 15፡18-19፣ 2ቆሮ. 12፡11-12
መሀመድ በቀልና ጥላቻን አስተምሯል ሱራ 2፡191-193፣ 8፡12፣ 8፡67፣ 8፡65፣ 9፡5፣ 9፡14፣ 9፡29፣ 9፡73፣ 9፡123፣ 48፡29፣ 58፡22
ጳውሎስ ሰዎችን ሁሉ ስለመውደድና አብሮ በሰላም ስለመኖር አስተምሯል ሮሜ 12፡18-19፣ 1ቆሮ. 13፡1-8
መሀመድ ዘራፊ ነበር ሱራ 8፡1
ጳውሎስ በገዛ እጆቹ እየሰራ ሌሎችን ይረዳ ነበር ሐዋ 18፡3፣ 20፡34፣
መሀመድ ለገዛ ጥቅሙ መገለጦችን ይናገር ነበር ሱራ 33፡50-51፣ 33፡37፣ 33፡53
ጳውሎስ ስለ ወንጌል ሲል ጥቅሙን አሳልፎ በመስጠት ብዙ መከራዎችን አሳልፏል 2ቆሮ. 11፡24-33
መሀመድ ውሸትን ፈቅዷል ሱራ 16፡106
ጳውሎስ ውሸታሞችን ተቃውሟል ቆላስይስ 3፡5-10፣ 2ቆሮ. 11፡13-15
መሀመድ ቅዱሳት መጻሕፍትን የማያውቅ መሐይም ነበር ሱራ 29፡48፣7:158
ጳውሎስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረ ሕግ አዋቂ ነበር ሐዋ. 22:3
መሀመድ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን የሚጠላ ሰው ነበር (ሱራ 5:60፣ 2፡65-66፣ 9፡29፣ Sahih Muslim, 698; SiIbn Ishaq, P. 464)
ጳውሎስ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን የሚወድ እስራኤላዊ ነበር ሮሜ 9፡1-5
መሀመድ መርዝ በልቶ ሞቷል (Sahih al-Bukhari Vol. 3, Bk 47, No. 786; Vol. 5, Bk 59, No. 713)